image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ የተከለከሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችና የፕላስቲክ ማምረቻ ግብዓቶችን አከማችቶ የተገኘ ድርጅት 50 ሺህ ብር ተቀጣ።

የካቲት 28, 2018
የልደታ ክ/ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ከፌዴራል የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር ባደረጉት ድንገተኛ ቁጥጥር 300 ኩንታል የተመረተ የተከለከለ የፕላስቲክ ከረጢት እና 300 ኩንታል ፕላስቲክ ለማምረት የሚያስችል ግብዓት አከማችቶ የተገኘ ድርጅት ላይ ህጋዊ እርምጃ ወስዷል። ጽ/ቤቱ የተከለከሉ የፕላስቲክ ምርቶችን የሚያምርቱ፣ ለገብያ የሚያቀርቡና ይዘው የተገኙ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ገልጿል። በአዋጅ ቁጥር 1383/2017 ማንኛውም ሰው/ድርጅት የፕላስቲክ ከረጢት ካመረተ ወይም ወደሃገር ውስጥ ካስገባ፣ ለገበያ ካቀረበ ወይም ከሸጠ፣ ለንግድ አላማ ካከማቸ ወይም ይዞ ከተገኘ ከ50 ሺ ብር የማያንስና ከ200ሺ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እና ከ5 አመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት እንደሚቀጣ ህጉ ይደነግጋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች