image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት ገር ገመገመ።

ግንቦት 1, 2018
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ እንደገለጹት ተቋሙ ዋና ተግባሩ ቁጥጥርና የክክትል ስራዎች ላይ አተኩሮ መስራት ነው ብለው በ9 ወራትም የአካባቢ ብክለት፣ በስርዓተ ምህዳርና ብዝሃ ህይወት ጥበቃ፣ በአካባቢ አጠባበቅ ላይ የክፍለ ከተማዋን ነዋሪ በማሳተፍ የግንዛቤ ማስጨበጫና ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። ኃላፊው አክለውም የክ/ከተማዋ አየር ንብረት ለማህበረሰቡ ተስማሚና ጤናማ እንዲሆን በቀጣይ ሰፊ ስራዎችንና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት እንደሚሰራ ገልጸው ሴክተር ተቋማት የአየር ንብረት ለውጥ ላይ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ተግባሮችን በእቅዳቸው አካተው በመስራት የበኩላቸውን እገዛ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ ተሳታፊዎቹም ጽ/ቤቱ የተሰጠው ተግባር እና ኃላፊነት ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተሳታፊ ለማረግ የሚያስችል በርካታ ስራዎች መስራት አለበት እንደ ባለድርሻ አካልም ሚናችንን እንወጣለን ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች