በልደታ ክ/ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ዋና ዋና አገልግሎቶች

1. በአካባቢ ብክለት እና ተጽእኖ ግምገማ ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
  • ስለአካባቢ ብክለት፣ህጎችና የአፈፃፀም መመሪያዎች ለህብረተሰቡ ስልጠናና ግንዛቤ መስጠት
  • ብክለት በሚያደርሱ ተቋማት ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ፣
  • የብክለት መጠን በመለካት እርምጃ መውሰድ ፣
  • የፕሮጀክቶችን የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሰነዶችን በመገምገምና መቆጣጠር የማስተካከያ ሀሳብ መስጠት
  • የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ እና የአካባቢ ተፅእኖ ክዋኔ ሪፖርት መከታተል
2. በአየር ንብረት ለውጥ ቡድን የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች
  • ስለአየር ንብረት ለውጥ፣ ህጎችና የአፈፃፀም መመሪያዎች ለህብረተሰቡ ስልጠናና ግንዛቤ መስጠት፣
  • ለአየር ንብረት ለውጥን በዘርፍ መ/ቤቶች በዕቅድ መካተቱን ማረጋገጥ ፣
  • ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ተጋላጭ የህበረተስብ ክፍሎች ድጋፍና ክትትል ፣
  • የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን የዲዛይንና የፕሮሞሽን ስራ በመስራት ለተጠቃሚዎች ማስፋፋት፥
3. በስርዓተ ምህዳርና ብዝሃ ህይወት አጠቃቀም እና ቁጥጥር ቡድን ስር የሚሰጡ አገልግሎቶች
  • በብዝሃ ህይወት ዙሪያ የተለያዩ የዳሰሳ ጥናቶችን መስራት እና ግኝታቸውን ለሚመለከተው አካል መላክ፤
  • በአረንጓዴ ቦታዎች ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ፡ የእጽዋት፤ ተባዮች፣ በሽታዎች፣ የእሳት አደጋዎች፣ መጤና ወራሪ አረሞችን በሁሉም የአረንጓዴ ቦታዎች ላይ ክትትል እና ቁጥጥር በመስራት ግብረ መልስ ለሚመለከተው ሪፖርት ይልካል፤
  • በአፈር መሸርሸር ምክንያት የተጎዳ ስርዓተ ምህዳርን በክትትል በመለየት ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያደርጋል፤
  • የችግኝ ጽድቀት መጠን ቆጠራ መስራት፤
  • አረንጓዴ ቦታዎች በህገ ወጥ መንገድ ወረራ እንዳይፈፀምባቸው እና ለታለመላቸው ዓላማ ስለመዋላቸው ቁጥጥር እና ክትትል ማድረግ፤
  • በአረንጓዴ መሰረተ ልማት እና ገፀ ምድር ማስዋብ ስራ ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ እና ለሚያማክሩ በዘርፉ ለተመረቁ ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ መስጠት፤
  • በሰው እና በዱር እንስሳት መካከል የሚነሳ ግጭትን ለማስቀረት የቅድመ ጥንቃቄ ትምህርት እና ግንዛቤ መስጠት፤
  • ለሚቀርቡ የዛፍ ምልመላ እና ቆረጣ ጥያቄዎች ፍቃድ እንሰጣለን፤ (ይዞታ ካላቸው ግለሰቦች፣ ድርጅቶች፣ ማህበራት፣ ተቋማት… ጥያቄዎች ሲቀርቡ)፤
  • ከሚቀርቡ የዛፍ ቆረጣ ፈቃድ የሮያሊቲ ገቢ መሰብሰብ፤
  • የደን ውጤቶች የይለፍ ፈቃድ መስጠት፤
  1. ገጽ-1
  2. ገጽ-2