ዜና | Oduu | News
በክፍለ ከተማው ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ

በልደታ ክ/ከተማ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥሉ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ ገለጹ። በክ/ከተማው በግንባታ ላይ የሚገኙ፣ የተጠናቀቁና አዳዲስ ሰው ተኮር እና የኢንሼቲቭ ስራዎችን ከምክር ቤት አባላት፣ ከመንግስት ሰራተኞች፣ ተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና በጎ የማህበረሰብ አንቂዎች የተውጣጣ ቡድን በመዘዋወር የመስክ ምልከታ አድርገዋል። የተከናወኑ የሰው ተኮር እና በኢንሼቲቭ የተሰሩ ልማት ስራዎች አስደናቂ ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን ወ/ሮ ልዕልቲ ገልጸዋል። የኢንሼቲቭ ስራዎቹ በተያዘላቸው እቅድ መሠረት መቀጠላቸውን ያነሱት ደግሞ የክ/ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አራርሳ ድሪባ ናቸው። አቶ አራርሳ አያይዘው በመስክ ምልከታው የግንባታ ስራቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑንና በስራ ላይ ያሉትም በጥራትና ፍጥነት እየተከናወኑ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል። አዳዲስ የኢንሼቲቭ ፕሮጀክቶች እና የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች እንዲሁም ነባር ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ በጥራት እየተከናወኑ መሆኑን ያረጋግጥንበት ነው ሲሉ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል። በክ/ከተማው ህዝቡን በማሳተፍ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እየቀጠሉ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ባለሃብቱንና ህብረተሰቡን በማስተባበር 58 የሚሆኑ የኢንሼቲቭ ስራዎች መሰራታቸውን በጉብኝቱ ወቅት ማየት ተችሏል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በልደታ ክፍለ ከተማ በአንድ ጀንበር ለ1500 ዜጎች የስራ ዕድል ትስስር ተፈጠረ።

በክ/ከተማው በአንድ ጀንበር ብቻ ለ1500 ዜጎች የስራ ዕድል ትስስር ተፈጥሯል። የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍታለው ከፍያለው እንደተናገሩት አስተዳደሩ የስራ ዕድል ፈጠራን የትኩረት ማዕከል አድርጎ በመስራት ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሯል ብለው በዛሬው ዕለት የተፈጠረው የስራ ዕድል ትስስር የዚሁ ማሳያ ነው ሲሉ ገልፀዋል። አቶ ፍታለው አክለውም የኢትዮጲያን የከፍታ ጉዞ ማረጋገጥ የሚቻለው ወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ሲቻል ነው ብለው ለዚህም አስተዳደሩ በትኩረት ይሰራል ሲሉ ተናግረዋል። የልደታ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አራርሳ ድሪብሳ በፕሮግራሙ ባስተላለፍት መልዕክት እንደተናገሩት በአንድ ጀንበር የስራ ዕድል ትስስር የተፈጠረላቸው 1500 ዜጎች በስራ ፈላጊነት ተመዝግበው ስልጠና የወሰዱ መሆናቸውን ገልፀው በዛሬው ዕለትም ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የቅጥር ውል እንዲፈራረሙ እና ወደ ስራ እንዲሰማሩ ተደርጓል ሲሉ ገልፀዋል። በ2018 በጀት ዓመት "በአዲስ ዕይታ የልደታንጰከፍታን ማረጋገጥ" የሚል መርህን ተላብሰን በሰራናቸው የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግባራት በርካታ የክ/ከተማችን ወጣቶችና ሴቶች ተጠቃሚ ሆነዋል ያሉት አቶ አራርሳ ለአብነትም የፈጠርናቸው የስራ ዕድሎች ማሳያ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል። አስተዳደሩ ለስራ ዕድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት በመስጠት ባለፍት 4 ወራት ብቻ ለ10 ሺህ 265 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩን ተገልጿል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በ2017ዓ.ም አፈጻጸም ከ11ዱም ክፍለ ከተማ 2ኛ ደረጃን በመያዝ የዋንጫ እና ሰርተፍኬት ተሻላሚ ሆነ.

የውጤት ዜና እንኳን ደስ አላችሁ!! እንኳን ደስ አለን!! የልደታ ክ/ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በ2017ዓ.ም አፈጻጸም ከ11ዱም ክፍለ ከተማ 2ኛ ደረጃን በመያዝ የዋንጫ እና ሰርተፍኬት ተሻላሚ ሆነ. ለዚህ ስኬትና ሽልማት እንድንበቃ ድጋፍና ክትትል እንዲሁም እገዛ ላደረጋችሁ የክፍለ ከተማው አስተባባሪ ኮሚቴ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ፣ ቡድን መሪዎች፣ ፈፃሚዎች ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባለው። ሽልማቱ ለቀጣይ በጀት ዓመት ለላቀ ትጋት የሚያነሳሳ በመሆኑ የልደታን ከፍታ እስከምናረጋግጥ በቀጣይም ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪዬን እያቀረብኩ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን ለማለት እወዳለሁ!! አቶ አንተነህ በፍቃዱ የልደታ ክ/ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
"በመትከል ማንሰራራት›" በሚል መሪ ቃል በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ በተገኙበት በልደታ ክ/ከተማ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄደ፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ እንደገለጹት አረንጓዴ አሻራ መካሄድ ከጀመረ ጀምሮ ሀገራችን በተለያዩ አረንጓዴ መስህቦች እየደመቀችና የአየር ንብረቷም እየተሻሻለ መምጣት ችሏል ያሉ ሲሆን ዘንድሮም በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል የጀመርነዉ ችግኝ መትከል ሁሉም ህብረተስብ በንቃት ሊሳተፍበትና የተከለዉን ችግኝም ሊንከባከበዉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ችግኝ በመትከል ሁሉም ዜጋ አሻራዉን ማሳረፍ ይጠበቅበታል በማለት የተናገሩት ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲስተካከልና የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ የአረንጓዴ ልማት ተግባራችን ማጠናከር የሁሉም ድርሻ ሊሆንም ይገባል ብለዋል፡፡ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በየአመቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር መካሄድ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እንደ ክፍለ ከተማችን ዉብ ሳቢና ማራኪ አካባቢን መፍጠር እየታቻለነው። እንዲሁም ክበባዊ አየሩም እንዲስተካከል ችግኝ ተከላዉ የራሱ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነዉ ይህም ከከተማና እስከ ሀገር ጥሩ ገጽታና አዲስ አበባን እንደስሟ አበባ ማድረግ የተቻለበት አጋጣሚ ነዉ ያሉ ሲሆን የክፍለ ከተማችን ነዋሪዎች በእዚህ የአረንጓዴ አሻራ ትግበራ ላይ እያሳያችሁት ያለዉ ንቁ ተሳትፎ የሚበረታታ ነዉ ተጠናክሮ ሊቀጥልም ይገባል ብለዋል፡፡

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክ/ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት ገር ገመገመ።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ እንደገለጹት ተቋሙ ዋና ተግባሩ ቁጥጥርና የክክትል ስራዎች ላይ አተኩሮ መስራት ነው ብለው በ9 ወራትም የአካባቢ ብክለት፣ በስርዓተ ምህዳርና ብዝሃ ህይወት ጥበቃ፣ በአካባቢ አጠባበቅ ላይ የክፍለ ከተማዋን ነዋሪ በማሳተፍ የግንዛቤ ማስጨበጫና ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል። ኃላፊው አክለውም የክ/ከተማዋ አየር ንብረት ለማህበረሰቡ ተስማሚና ጤናማ እንዲሆን በቀጣይ ሰፊ ስራዎችንና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት እንደሚሰራ ገልጸው ሴክተር ተቋማት የአየር ንብረት ለውጥ ላይ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ተግባሮችን በእቅዳቸው አካተው በመስራት የበኩላቸውን እገዛ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ ተሳታፊዎቹም ጽ/ቤቱ የተሰጠው ተግባር እና ኃላፊነት ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተሳታፊ ለማረግ የሚያስችል በርካታ ስራዎች መስራት አለበት እንደ ባለድርሻ አካልም ሚናችንን እንወጣለን ብለዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
"በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል የክረምት በጎ ፈቃድ ደም ልገሳ ተደረገ

"በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል የክረምት በጎ ፈቃድ ደም ልገሳ ተደረገ የልደታ ክ/ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሄደ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወት እንታደግ በማለት የሚሰበሰበው ደም በተለያዩ ምክንያቶች ደም ለሚስፈልጋቸው ዜጎቻችን እንደሚውል በመግለፅ አንድ ሰው የሚለግሰው ደም ሰዎችን ህይወት መታደግ ያስችላል በፕሮግራሙ ላይ የደም ለጋሽ ማህበሩ አባላትና በጎፈቃደኞች ተገኝተው የመለገስና የማስለገስ ስራ ተሰርቷል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች፣ የኅብረተሰብ ተሳትፎ እና የበጎ ፍቃድ ሥራዎች የ90 ቀናት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

የክፍለ ከተማው አስተዳደር በቀጣይ ዘጠና ቀናት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ፤በህብርተሰብ ተሳትፎ እና የበጎ ፍቃድ ስራዎች የንቅናቄ እቅድ ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ የግብረ ሀይል አባላት በተገኙበት ውይይት ተካሔዷል፡፡ በውይይቱ የክፍለ ከተማው አካባቢ ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ የቀጣይ ዘጠና ቀናት እቅድን አቅርበው ውይይት ተካሄዶበታል፡፡ የክፍለ ከተማው የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ እጅጋየሁ አድማሱ ውይይቱን በመሩበት ወቅት እንደገለጹት ተግባራቱን በጥብቅ ዲስፒሊን መምራት ወረዳዎችና ተቋማት ነባራዊ ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ እቅዱን መፈጸም እንደሚገባቸው አንስተዋል፡፡ በክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ተቋማት የተግባሩ ባለቤት በማድረግ መስራት እና ቴክኒካል ድጋፍ ማድርግ እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡ ብሎኮች በሁሉም መመዘኛ መስፈርቶች ሞዴል መሆን እንዳለባቸው ያነሱት ወ/ሮ እጅጋየሁ በተለይም በጽዳት፤በውበት ስራ በሁሉም ብሎኮች የሚገኙ ቤቶች መብራት እንዲያወጡ ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል ፤የበጎ ፍቃድ የቤት ግንባታና እድሳት በተያዘላቸው እቅድ መሰረት መፈጸም እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡ ከሰኔ 5 እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2017 ተግባራዊ በሚደረገው የ90 ቀናት ዕቅድ በኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት፣ በመሠረተ ልማት፣ በጽዳት፣ በአደጋ መከላከል፣ በከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት እንዲሁም ሌሎች መስኮች በርካታ ሥራዎችን ለማከናወን የታቀደ መሆኑ በመድረኩ ላይ የተገለጸ ሲሆን፣ እነዚህን ተግባራት ለማከናወን የሚያስችል ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱ ተገለፀ። በቀረበው እቅድም በቀጣይ ዘጠና ቀናት የክረምት በጎ ፍቃድ በተቀናጀ አግባብ መምራት፤የከተማ ፅዳትና የውበት ስራዎች፤የአደጋ ስጋት መለየት መከላከል/ተረጂነትን መቀነስ/፤የፋይዳ ምዝገባን ማሳደግ፤በመስከረም ወር የሚከበሩ በአላት ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ባጠናከረ መልኩ እንዲከበሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን መከወን፤ የክረምት የአረንጓዴ አሻራ በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተመላክቷል፡፡

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ጽ/ቤቱ የወንዝ ዳርቻ ጥበቃና ክልከላ የደንብ ቁጥር 180/2017 የተመለከተ የውይይት መድረክ አካሂዷል።

የህግ ጉዳይችንና መመሪያዎች ለህብረተሰቡ በማስገንዘብ ዜጎችን ከአላስፈላጊ ቅጣቶችና ርምጃዎች ለመጠበቅ እየሰሩ መሆኑን የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ገለጸ። የልደታ ክፍለ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጋሻዬነህ ታፈሰ እንደተናገሩት በአዲስ አበባ የከተማዋን ገጽታ የሚለውጡና የሚያሳምሩ እንዲሁም የህብረተሰቡን የረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚመልሱ የልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው የሚሰሩ የልማት ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ወንዞችን በንጽህና መያዝና የወንዝ ዳርቻውዎችን ከብክለት መከላከል ይገባል ብለዋል። አቶ ጋሻዬነህ አክለውም የህግ ጉዳዮችንና መመሪያዎችን ለህብረተሰቡ በማስገንዘብ ከአላስፈላጊ ቅጣትና እርምጃዎች ለመጠበቅ፣ህግ የሚተላለፉትን ደግሞ አስተማሪ ቅጣት እንደሚቀጣ ገልጸው የደንብ ቁጥር 180/2017 መሠረት በወንዝ ዳርቻዎች ላይ በሚሰሩ ስራዎችና በወንዞች ጉዳት የሚያደርሱ አካላትን ጥቆማ በመስጠት ተጠያቂነትን ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል። ልማቶች በተለይም በወንዝ ዳርቻወች የሚከናወኑ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑና ለረጅም ዓመታት ህብረተሰቡን መጥቀም እንዲችሉ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች በህብረተሰቡ ሊጠብቁ እንደሚገባ የገለጹት አቶ ጋሻየነህ ከተለያዩ ተቋማት የሚወጡ በካይ ፍሳሽና ኬሚካሎች፣ያለፈቃድ የታከመ ፈሳሽን ወደ ወንዝ መልቀቅ፣በካይ ፍሳሽን ከጎርፍ መውረጃ ጋር ማገናኘት እንዲሁም ኬሚካል ነክ ፍሳሾችን የማከሚያ ዘዴን ሳይጠቀሙና ሳይረጋገጥ ወደ ወንዝ መልቀቅ በወንዝ ዳርቻ ጥበቃና ክልከላን የተመለከተውን የደንብ ቁጥር 180/2017 መሠረት የተከለከለ መሆኑን በመገንዘብ ነዋሪዎችና ባለድርሻ አካላት የመመሪያውን ተግባራዊነት እንዲረጋገጥ በመተባበር መስራትይገባል ብለዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የ6 ወር አፈፃፀም ምዘና 97% በማምጣት 2ኛ ደረጃ በመያዝ ተሸላሚ ሆኗል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በግማሽ ዓመቱ ባካሄደው ምዘና የልደታ ክ/ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት 97% በማምጣት በተግባር አፈፃፀም ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች መካከል 2ተኛ ውጤት በማስመዝገብ ተሸላሚ ሆኗል:: የልደታ ከተማ ክ/ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ ይህን ውጤት እንዲመጣ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላደረጉ የክፍለ ከተማው አስተባባሪ ኮሚቴ አባላትና ለሁሉም አመራሮች ለጽ/ቤቱ ቡድን መሪዎችና ፈፃሚዎች እንዲሁም ለወረዳዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
"የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማት እና ከብክለት በመከላከል ውብ ፅዱ እና ለኑሮ ተስማሚ አካባቢን እውን ማድረግ ይኖርብናል" ወ/ሮ አበባ እሸቴ።

"የከተማችን ወንዞች ተጨማሪ የውበት ነፀብራቅ እንጂ የጤና ጠንቅ ሊሆኑ አይገባም" አቶ ሃፍቱ ብርሀኑ የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር "ንፁህ ወንዞች ፤ለጤናማ ህይወት"በሚል መሪ ቃል የወንዝ ዳርቻ ልማትና ብክለት መከላከል ደንብ ቁጥር 180/2017 ዙሪያ ለአመራሩ የንቅናቄ ማስጀመሪያና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሂዷል። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በመድረኩ ባስተላለፍት መልዕክት የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማት እና ከብክለት በመከላከል ውብ ፅዱና ለኑሮ ተስማሚ አካባቢን መፍጠር ይገባል ብለው የወንዝ ዳርቻዎችን ከብክለት መከላከልና ወንዞችን ማልማት የሁሉም ዜጋና የተቋማት ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። ከተማችንን የበለጠ ውብ ፅዱና አረንጓዴ ለማድረግ የወንዝ ዳርቻ ልማት ወሳኝነት አለው ያሉት ወ/ሮ አበባ ወንዞችን ከብክለት መከላከል እና የወንዝ ዳርጃዎችን ማልማት ትኩረት ተሰጥቶበት እየተከናወነ ያለ ተግባር መሆኑን በማንሳት ማህበረሰቡና ተቋማት ቆሻሻን ወደ ወንዝ ከመልቀቅ ሊታቀቡና መንግስት እያከናወነ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ልማት ሊያግዙ ይገባል በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃፍቱ ብርሀኑ እንደተናገሩት የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማትና ከበካይ ነገሮች በመከላከል ወንዞች የከተማችን ተጨማሪ የውበት ነፀብራቅ እንጂ የጤና ጠንቅ እንዳይሆኑ መስራት ይኖርብናል ብለዋል። መንግስት ከተማችንን ውብ ፅዱና ለነዋሪዎች እንዲሁም ለጎብኝዎች ምቹ ለማድረግ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ የወንዝ ዳርቻ ልማትና ወንዞችን ከብክለት የመከላከል ተግባር መሆኑን የገለፁት አቶ ሃፍቱ ማህበረሰቡም ሆነ ተቋማት ወንዞችን በመጠበቅ ረገድ የድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል። የክ/ከተማው የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ የወንዝ ዳርቻዎችን የማልማት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ማህበረሰቡ ወንዞችን ከባይ ነገሮች በመጠበቅ አገራዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። አቶ አንተነህ አክለውም የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ እና የቁጥጥርና የክትትል ስራን ማጠናከር በትኩረት ይሰራበታል ብለው ግንዛቤ ተፈጥሮላቸው ላልታረሙ ተቋማትና ግለሰቦች በደንቡ መሰረት እንደሚቀጡ ገልፀዋል። ተሳታፊዎች በበኩላቸው የወንዞችን ንፅህና መጠበቅ ጤናማ የሆነ ማህበረሰብ ለመገንባት ያስችላል ብለው የወንዞችን ንፅህና በመጠበቅና በማስጠበቅ ረገድ አመራሩ የድርሻውን ይወጣል ማህበረሰቡም አጋዥ ሊሆን ይገባል በማለት ተናግረዋል። የክ/ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤትና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ለደንብ ቁጥር 180/2017 ተፈፃሚነት በትጋት እንደሚሰሩም ተገልጿል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የአካባቢ እና የወንዞች ብክለት በመቀነስ ውብ፣ ጽዱና ለኑሮ ምቹ አካባቢ በመፍጠር ተግባራትን አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ::

አቶ አንተነህ በፍቃዱ የልደታ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ ጽ/ቤት በፕላን ማናጅመንት እና በ180/2017 ደንብ ዙርያ ለሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች እና የምግብ ቤት ባለቤቶች የግንዛቤ ማስጨበጪያ ስልጠና ሰጠ የልደታ ክፍለ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ የፍሳሽ እና የቆሻሻ አወጋገድ እና በአካባቢ ብክለት እየተስተዋሉ ያሉ የጽዳት ችግሮች በአፋጣኝ ማረም እንደሚገባ በመግለፅ የአካባቢ የወንዞች ብክለት በመቀነስ ውብ፣ ጽዱና ለኑሮ ምቹ አካባቢ ለመፍጠር ተግባራትን ከናንተ ጋር በጋራ አጠናክሮ መስራት ይገባል ብለዋል። አካባቢ ጥበቃ ስራ መስራት እጅግ ወሳኝና ግዴታም ነው ያሉት አቶ አንተነህ ተግባሩ በኃላፊነት፣በቁርጠኝነት እና በህግና በመመሪያ መሰረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። ተሳታፊዎች ጹዱ ከአካባቢ ከብክለት የፀዱ ወንዞችን ለመፍጠር በከተሞች አካባቢ የቆሻሻ አወጋገድ ችግር ይስተዋላል በማለት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት የማድረግ እና አካባቢን እና ወንዞችን ከሚበክል ተግባራት እራሳቸው እንዲቆጠብ በመግለፅ አካባቢ የሚበክል ተግባር የሚተገብሩት ላይ በደንቡ መሰረት የማስተካከያ እርምጃ ከመውሰድ ጋር የተጀመሩ ስራዎች ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

image
image
image
image