image
image
image
image
image

የአካባቢ እና የወንዞች ብክለት በመቀነስ ውብ፣ ጽዱና ለኑሮ ምቹ አካባቢ በመፍጠር ተግባራትን አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ::

መጋቢት 10, 2018
አቶ አንተነህ በፍቃዱ የልደታ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ ጽ/ቤት በፕላን ማናጅመንት እና በ180/2017 ደንብ ዙርያ ለሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች እና የምግብ ቤት ባለቤቶች የግንዛቤ ማስጨበጪያ ስልጠና ሰጠ የልደታ ክፍለ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አንተነህ በፍቃዱ የፍሳሽ እና የቆሻሻ አወጋገድ እና በአካባቢ ብክለት እየተስተዋሉ ያሉ የጽዳት ችግሮች በአፋጣኝ ማረም እንደሚገባ በመግለፅ የአካባቢ የወንዞች ብክለት በመቀነስ ውብ፣ ጽዱና ለኑሮ ምቹ አካባቢ ለመፍጠር ተግባራትን ከናንተ ጋር በጋራ አጠናክሮ መስራት ይገባል ብለዋል። አካባቢ ጥበቃ ስራ መስራት እጅግ ወሳኝና ግዴታም ነው ያሉት አቶ አንተነህ ተግባሩ በኃላፊነት፣በቁርጠኝነት እና በህግና በመመሪያ መሰረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል። ተሳታፊዎች ጹዱ ከአካባቢ ከብክለት የፀዱ ወንዞችን ለመፍጠር በከተሞች አካባቢ የቆሻሻ አወጋገድ ችግር ይስተዋላል በማለት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት የማድረግ እና አካባቢን እና ወንዞችን ከሚበክል ተግባራት እራሳቸው እንዲቆጠብ በመግለፅ አካባቢ የሚበክል ተግባር የሚተገብሩት ላይ በደንቡ መሰረት የማስተካከያ እርምጃ ከመውሰድ ጋር የተጀመሩ ስራዎች ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች