image
image
image
image
image

የልደታ ከተማ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር አፈፃፀም ከባለድርሻ አካላት ጋር ግምገማ አካሄደ፡፡

ጥር 15, 2018
የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የማህበረሰብ ተሳትፎ ያለው ሚና ጉልህ መሆኑ ተገለፀ። የልደታ ክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ቅባት ገ/ክርስቶስ በጽ/ቤቱ በግማሽ ዓመቱ ውስጥ በርካታ ስኬታማ ተግባራት መሰራታቸውን ገልፀው የአየር ንብረት ለውጥና አያያዝን ለማህበረሰቡ ተከታታይነት ያለው ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች መሰራቱን ገልፀዋል። የአካባቢ ብክለትን ለመቀነስ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን የገለፁት ወ/ሮ ቅባት አያይዘው የአካባቢ ብክትን ከመቀነስ አንፃርም ሆነ የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ በማፅደቅ ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት በመስራታችን የተሻለ ውጤት ማስመዝገቡን ገልፀዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም በአካባቢ ብክለት ዙሪያ የተሻለ ግንዛቤ መፈጠሩ የተሻለ መሆኑንን በመግለፅ የተሻለ ስራ መሰራቱን አንስተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች