image
image
image
image
image

የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች፣ የኅብረተሰብ ተሳትፎ እና የበጎ ፍቃድ ሥራዎች የ90 ቀናት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

ሰኔ 11, 2018
የክፍለ ከተማው አስተዳደር በቀጣይ ዘጠና ቀናት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ፤በህብርተሰብ ተሳትፎ እና የበጎ ፍቃድ ስራዎች የንቅናቄ እቅድ ላይ የክፍለ ከተማና የወረዳ የግብረ ሀይል አባላት በተገኙበት ውይይት ተካሔዷል፡፡ በውይይቱ የክፍለ ከተማው አካባቢ ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንተነህ የቀጣይ ዘጠና ቀናት እቅድን አቅርበው ውይይት ተካሄዶበታል፡፡ የክፍለ ከተማው የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ እጅጋየሁ አድማሱ ውይይቱን በመሩበት ወቅት እንደገለጹት ተግባራቱን በጥብቅ ዲስፒሊን መምራት ወረዳዎችና ተቋማት ነባራዊ ሁኔታን ባገናዘበ መልኩ እቅዱን መፈጸም እንደሚገባቸው አንስተዋል፡፡ በክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ተቋማት የተግባሩ ባለቤት በማድረግ መስራት እና ቴክኒካል ድጋፍ ማድርግ እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡ ብሎኮች በሁሉም መመዘኛ መስፈርቶች ሞዴል መሆን እንዳለባቸው ያነሱት ወ/ሮ እጅጋየሁ በተለይም በጽዳት፤በውበት ስራ በሁሉም ብሎኮች የሚገኙ ቤቶች መብራት እንዲያወጡ ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል ፤የበጎ ፍቃድ የቤት ግንባታና እድሳት በተያዘላቸው እቅድ መሰረት መፈጸም እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡ ከሰኔ 5 እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2017 ተግባራዊ በሚደረገው የ90 ቀናት ዕቅድ በኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት፣ በመሠረተ ልማት፣ በጽዳት፣ በአደጋ መከላከል፣ በከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት እንዲሁም ሌሎች መስኮች በርካታ ሥራዎችን ለማከናወን የታቀደ መሆኑ በመድረኩ ላይ የተገለጸ ሲሆን፣ እነዚህን ተግባራት ለማከናወን የሚያስችል ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱ ተገለፀ። በቀረበው እቅድም በቀጣይ ዘጠና ቀናት የክረምት በጎ ፍቃድ በተቀናጀ አግባብ መምራት፤የከተማ ፅዳትና የውበት ስራዎች፤የአደጋ ስጋት መለየት መከላከል/ተረጂነትን መቀነስ/፤የፋይዳ ምዝገባን ማሳደግ፤በመስከረም ወር የሚከበሩ በአላት ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ባጠናከረ መልኩ እንዲከበሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን መከወን፤ የክረምት የአረንጓዴ አሻራ በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተመላክቷል፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች